Types of Amharic PRONOUN // Ye Amargna sewasew / Learn Amharic Easily

Types of Amharic PRONOUN // Ye Amargna sewasew / Learn Amharic Easily

የተውላጠ ስም ዓይነቶች (KINDS OF PRONOUN) ዋናዋና የተውላጠ ስም ክፍሎች ቀጥለው የቀረቡት አራቱ ናቸው፦ The main types of Amharic pronouns are four:

  1. መደብ ተውላጠ ስም (Personal pronoun)
  2. ጠቋሚ ተውላጠ ስም (Demonstrative pronoun)
  3. አዛማጅ ተውላጠ ስም (Relative pronoun)
  4. መጠይቅ ተውላጠ ስም (Interrogative pronoun)

መደብ ተውላጠ ስም (Personal pronoun) ደግሞ በአራት ይከፈላል። (Personal pronouns are divided into four categories.)

  1. ባለቤት ተውላጠ ስሞች (Subjective pronouns)
  2. ተሳቢ /ድርጊት ተቀባይ ተውላጠ ስሞች (Objective pronouns)
  3. አገናዛቢ ተውላጠ ስሞች (Possessive pronouns)
  4. ድርብ /አፀፋ ተውላጠ ስሞች (Reflexive pronouns)

ባለቤት ተውላጠ ስሞች የሚባሉት ቀጥለው የቀረቡት 10 ቃላት ናቸው። The next 10 words are called Subjective pronouns.

ባለቤት ተውላጠ ስሞች Subjective pronouns
እኔ I
እኛ We
አንተ You (for male)
አንች You (for female)
እናንተ You (for plural)
እርስዎ / እርሳቸው/አንቱ You (Formal, to respect the elders)
እሱ He
እሷ She
እነሱ They
እንትን It

የባለቤት ተውላጠ ስሞች ሌላ ስማቸው አድራጊ ተውላጠ ስሞች” ነው። ባለቤት ተውላጠ ስሞች ከማንኛውም ግስ በፊት ቀድመው በመግባት ድርጊት ይፈፅማሉ። ለምሣሌ፦

  • Another name for “ባለቤትነት ተውላጠ ስም” is አድራጊ ተውላጠ ስሞች” Subjective pronouns come before any verb to perform an action. For example:

ፋጢማ ድመቶችን ትወዳለች። እሷ አራት ድመቶች አሏት። (Fatima likes cats. She has four cats.)                                      

  • “ፋጢማ (Fatima)” የሚለው የተፀውኦ ስም “ትወዳለች (likes)” ከሚለው ግስ በፊት ገብቷል። (The noun “Fatima” comes before the verb “likes”.)
  • “እሷ (She)” የሚለው ባለቤት ተውላጠ ስም “አሏት (has)” ከሚለው ግስ በፊት ገብቷል። (The Subjective pronoun “she” comes before the verb “has”.)

ተሳቢ ተውላጠ ስሞች (Objective pronouns)

ተሳቢ ተውላጠ ስሞች የሚባሉት ድርጊቱ የሚፈጽምባቸው የተውላጠ ስም ክፍሎች ናቸው። እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

Objective pronouns are the parts of the pronoun which are the action happens on. They are as follows:

ተሳቢ ተውላጠ ስሞች (Objective pronouns)
እኔን /ለኔ Me
አንተን /ላንተ You
አንችን /ላንች You
እናንተን /ለናንተ You
እሱን /ለሱ Him
እሷን /ለሷ Her
እሱን /ለሱ /እሷን /ለሷ It
እኛን /ለኛ Us
እነሱን /ለነሱ Them

ምሣሌ፦

ፋጢማ ድመቶች ትወዳለች። እሷ እነሱን ማሻሸት ያስደስታታል። (Fatima likes cats. She likes to stroke them.)                                      

“ድመቶች /Cats” የሚለው ስም “ትወዳለች (likes)” የሚለው ግስ ተሳቢ ወይም ድርጊት ተቀባይ ነው።

Here the objective noun is “ድመቶች (Cats)” and the verb is “ትወዳለች (likes)”. The action applies on the objective nouns.

An other ለምስሌ፦

If I say, “ፋጢማ ድመቶቹ ትመታቸዋለች።” (Fatima beats the cats.) In this sentence, Fatima is the doer of the action and the cats are the victims of the action. Here it is the letter “” that shows us that the word ድመቶቹ is the victim of the action. If it were just “ድመቶቹ” it would be just a noun. When we add the letter “” at the end of any noun, the word becomes an objective noun.

 Example:

ስሞች ተሳቢ ስሞች
ድሃ

Poor

ድሃን አብላ።

Feed the poor.

ለማኝ

Beggar

ለማኝንም አትገላምጥ፡፡

Nor repulse the beggar;

ድመት

Cat

ድመቷን ምግብ ስጣት።

Give the cat some food.

ውሻ

Dog

ውሻውን ከዚህ አባረው።

Get the dog away from here.

ውሃ

Water  

ውሃውን ስጠኝ።

Give me the water.

አልጋ

Bed

አልጋህን አንጥፈው።

Make your bed.

ቲቪ

Tv

ቲቪውን ዝጋው።

Swich off the Tv.

ኮምፒውተር

Computer  

ኮምፒውተሩን አብራው።

Turn on the computer.

በሬ

Bull

በሬውን ሽጠው።

Sell the bull.

 

ፋጢማ ድመቶቹን ትመታቸዋለች። ብንል፣ በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ድርጊቱን ፈፃሚዋ ፋጢማ ስትሆን ድርጊቱ የሚርፍባቸው ደግሞ ድመቶቹ ናቸው። እዚህ ጋ ድመቶቹ የሚለው ቃል ድርጊት ተቀባይ መሆኑን የምታሳየን “ን” የምትለዋ ፊደል ናት። “ድመቶቹ” ብቻ ቢሆን ኖሮ ስም ብቻ ይሆን ነበር። ስሙ መጨረሻ ላይ “ን” ፊደል ስንጨምርበት ቃሉ ድርጊት የሚፈጸምበት ይሆናል።

በሁለተኛው ዓረፍተ ነገር ውስጥ ደግሞ “እነሱን (them)” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም “ማሻሸት (stroke)” የሚለው ግስ የሚያርፍበት ድርጊት ተቀባይ ነው።

አገናዛቢ ተውላጠ ስም (Possessive pronoun)

አገናዛቢ ተውላጠ ስሞች እንደ አገናዛቢ ቅጽል የራስ የሆነን ነገር ይጠቁማሉ። እነሱም እንደሚከተለው ቀርበዋል።

አገናዛቢ ተውላጠ ስም (Possessive pronoun)
የራሴ/ የኔ Mine
የራሳችን/ የእኛ Ours
የራስህ/ ያንተ Yours
የራስሽ/ያንቺ Yours
የራሳችሁ/የናንተ Yours
የራሱ/ የእሱ His
የራሷ/ የእሷ Hers
የራሳቸው/ የነሱ Theirs

እነዚህ አገናዛቢ ተውላጠ ሰዎች በአንድ ነገር ዙሪያ “የኔ ነው / ያንተ አይደለም” እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ የሚጠቀሟቸው ቃላት ናቸው። ምሳሌ፦

  • ይህች የራሴ ድመት ናት ያንተ አይደለችም። (This cat is mine not yours.)
  • እሱ የኔ አይደለም፣ የራስህ ነው። (It is not mine, it is yours.)
  • ይህ ቦታ የራሳቸው ነው። (This place is theirs.)

ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውንና ብዙውን ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቃላትን ቀጥለን እንማር፦

Let’s continue with similar and frequently used words:

የኔን ስጠኝ Give me mine
ገንዘቤን ስጠኝ Give me my money
የራሴን ገንዘብ ስጠኝ Give me my own money
የሱን ስጠው Give him his
ገንዘቡን ስጠው Give him the money
የሷን ስጣት Give her hers
ገንዘቡን ስጣት Give her the money
የራሷን ገንዘብ ስጣት Give her her own money
ገንዘባቸውን ስጣቸው Give them their money

ሰዎች በጣም ሲናደዱም “የራስ” የሚለው ቃል ላይ “ጉዳይ” የሚለውን ቃል በመጨመር ይናገሩታል።ለምሳሌ፦

  • የራሱ ጉዳይ ባክህ
  • የራስህሽ ጉዳይ
  • የራስህ ጉዳይ
  • የራሳችሁ ጉዳይ
  • የራሷ ጉዳይ ባክህ
  • የራሳቸው ጉዳይ ባክህ እኔ ስለነሱ አያገባኝም።

የራሱ ጉዳይ ማለት “አያሳስበኝም፣ ተወው፣ ተይው አትጨነቂ ወዘተ” ማለት ነው።

አገናዛቢ ቅጽሎች (Possessive adjectives)

አገናዛቢ ቅጽሎች ስም ገላጭ ናቸው ማለትም ስሙን የሚገልጹት የማን እንደሆነ ወይም ለማን እንደሚገባ በማመልከት ነው። አገናዛቢ ቅጽሎች የተውላጠ ስም ክፍሎች አይደሉም፣ የገላጭ ክፍሎች ናቸው፣ እዚህ ያቀርብኳቸው ቃላቱ ተመሳሳይነት ስላላቸው ነው። አገናዛቢ ቅጽሎች የሚከተሉት ናቸው፦

My የኔ
Your ያንተ/
Your ያንች
Your የናንተ
His የሱ
Her የሷ
Its የሱ/የሷ
Our የኛ
their የነሱ

መልመጃ 6

Can you use the pronouns we’ve seen so far correctly? Test your understanding with this practice question. Fill in the blank by choosing the correct personal pronoun or possessive adjectives.

እስካሁን ከዚህ በላይ ያየናቸውን ተውላጠ ስሞች በትክክል መጠቀም ይችላሉ? እስቲ በዚህ የመልመጃ ጥያቄ ግንዛቤዎን ይፈትሹ። ትክክለኛውን መደብ ተውላጠ ስም ወይም አገናዛቢ ቅጽል በመምረጥ ክፍት ቦታውን ይሙሉ።

1.___ ሳሙኤል ይባላል። ___ ጀርመናዊ ነኝ።

A. ስሜ & እኔ    B. እኔ & ነኝ     C.  ስሙ & እሱ   D.    የኔ ስም & እኔ

2. አያቶቼ በርሊን ውስጥ ይኖራሉ።___ ብዙ ጊዜ እንጎበኛቸዋለን። 

A. እኔ           C.  እነሱ             B.        እኛ

3. ____ትናንትና ___አይተኸኛል? 

A. እሱ & እነሱን      B.   አንተ & እሱን     

C.     እኔ & አንተን   D. አንተ & እኔን

4.___ተምታቶብኝ ስለ ነበር ጥያቄውን ልመልሰው አልቻልኩም።

A.     እኛ             B.    እሷ             

C.     አንተ            D.    እኔ

5. ይህ ብዕር ___ ነው። የርስዎ አይደለም።                                                                                                                                                                                                                      A. የኔ / የራሴ         C.       የእርሱ / የእርሷ   

B.    A & C       D.    None of the above

6. ይህ መኝታ ቤት ___ ነው። ያ የሷ ነው።

A. የኔ             C.         የነሱ ያንተ D.        ሁሉም መልስ ነው

7. ለዚህ ለዚህ ___ባለንበት እንቆይ።

A. እኔ         B.    እኛ 

C.  እነሱ      D.    እሷ

8.___ላሞቻቸውን በቀን ሁለት ጊዜ ያልባሉ። እኛ                   

A.    የነሱ     B.   እነሱ     C.    እኔ

አፀፋ ወይም ድርብ ተውላጠ ስም (Reflexive pronoun)

ድርብ ተውላጠ ስም የተባሉበት ምክንያት በመደበኛው ተውላጠ ስም ላይ እየተደረቡ ሥለሚገቡ ነው። ለምሣሌ፦

 

The reason why they are called double pronouns is that they are placed on top of regular pronouns. For example: አፀፋ ተውላጠ ስሞች ወጥለው ቀርበዋል፦

አፀፋ ወይም ድርብ ተውላጠ ስም (Reflexive pronoun)
ራሴ Myself
ራስህ/ራስሽ Yourself
ራሱ Himself
ራሷ Herself
ራሱ/ራሷ Itself
ራሳችን Ourselves
ራሳችሁ Yourselves
ራሳቸው Themselves

አፀፋ ተውላጠ ስሞች (Reflexive pronouns)

ምሣሌ

  • አንተው ራስህ ልትሰራው ትችላለህ። You can do it yourself
  • እሱ ራሱን እና ሌሎችን ይረዳል። He treats himself and others.
  • እሷ በአንድ አሰቃቂ ቀን ራሷን ወንበሯ ላይ ቁጭ ብላ አገኘችው። She found herself one dready day sitting at her desk.
  • ድመታችን ምግብ ከበላች በኋላ ራሷን ታጥባለች። Our cat washes itself after each meal.
  • እናንተ በራሳችሁ መተማመን አለባችሁ። You have to believe in yourselves.
  • እኛ ብቻችንን ማውራት እንችላለን? Can we talk by ourselves?
  • እነሱ የሚያስቡት ስለራሳቸው ነው። They think about themselves.

መልመጃ 7፦

የጎደለውን ባዶ ቦታ በትክክለኛው አፀፋ ተውላጠ ስም (Reflexive pronoun) ይሙሉ። Fill in the blanks with the correct reflexive pronoun.

  1. እኔ ___እሰራዋለሁ። I will do it___.
  2. ልብሱን እሷ ___ሰፋችው። She made the dress by___.
  3. ወሬውን እሱ ____ነገረኝ። He___tolled me the news.
  4. ጎጆውን እሱ ____ነው የሰራው። He built the shed by____.
  5. ይሄ ____ችሎ መቆም አይችልም። This cannot stand by____.
  6. አንተው ____ነህ እንደዚያ ያልከው። You____said so.
  7. አንችው ____ነሽ እነዚህን የእጅ ሹራቦች የጠለፍሻቸው? Did you knit these gloves___?
  8. ቤቱን እኛው____ ነን ቀለም የቀባነው። ማንም የረዳን ሰው የለም። We painted the house____. Nobody helped us.
  9. እናንተ ለምን _____ትወቅሳላችሁ? Why do you blame____?
  10. እነሱ _______ይህንን ስህተት ብዙ ጊዜ ፈፅመውታል። They_____have made that mistake several times.

ጠቋሚ ተውላጠ ስም (Demonstrative pronoun)

ጠቋሚ ተውላጠ ስሞች ወደ አንድ ነገር ለመጠቆም የሚያገለግሉ ሲሆን፣ እነሱም ቀጥለው ቀርበዋል፦

ይህ This
That
እነዚህ These
እነዚያ Those

ጠቋሚ ተውላጠ ስሞች (Demonstrative pronouns)

Demonstrative pronouns                  (ጠቋሚ ተውላጠ ስሞች)  

 

አገልግሎት

 

 

ምሣሌ፦

       ይህ This   

        ያ  That   

እነዚህ ጠቋሚ ተውላጠ ስሞች ነጠላ ስሞችን ለመጠቆም ያገለግላሉ። ይህ እኔ የምፈልገው ዘገባ ነው።This is the report I want.                                    

በጣም የሚገርም ነው! That is amazing!                              

       እነዚህ These

        እነዚያ Those

ብዙ ስሞችን ለመጠቆም ያገለግላሉ። እነዚህ ልጆቻችን ናቸው። These are our children.                       

እነዚያ ቤተሰቦቻችን ናቸው።Those are our families.                 

        ይህ This 

       እነዚህ These 

በቅርብ ቦታ ላይ ያለን ነገር ለመጠቆም ያገለግላሉ። እሱ ይህንን ሰጠኝ።

He gave me this.                    እነዚህ መኪናዎቼ ናቸው።These are my cars.                  

       That   

       እነዚያ Those 

በሩቅ ቦታ ወይም ጊዜ ላይ የሚገኝን ነገር ለመጠቆም ያገለግላሉ። ያንን ተመልከት። Look at that.                        

እነዚያ መጥፎ ቀናቶች ነበሩ።Those were bad days.

መልመጃ 7 ፦

የጎደለውን ባዶ ቦታ በትክክለኛው አፀፋ ተውላጠ ስም ይሙሉ።

  1. እኔ ____እሰራዋለሁ። I will do it   .                                                                                                                     
  2. ልብሱን እሷ ___ሰፋችው። She made the dress by____.
  3. ወሬውን እሱ ራሱ ነገረኝ። He told me the news.                                                                                        
  4. ጎጆውን እሱ ብቻውን ሰራ። He built the shed by____.
  5. ይሄ _____ችሎ መቆም አይችልም። This cannot stand by .                                                                                                       
  6. አንተው ____ነህ እንደዚያ ያልከው። You said so.                                                                                                      
  7. እነዚህን የእጅ ሹራቦች አንችው _____ነሽ የጠለፍሻቸው? Did you knit these gloves ?                                                                                 
  8. ቤቱን እኛው _____ነን ቀለም የቀባነው። ማንም የረዳን ሰው የለም። We painted the house . Nobody helped us.                                                                  
  9. እናንተ ለምን _____ትወቅሳላችሁ? Why do you blame ?                                                                                           
  10. እነሱ ______ይህንን ስህተት ብዙ ጊዜ ፈፅመውታል። They have made that mistake several times.                                                                     

Relative pronoun (አዛማጅ ተውላጠ ስም)                                            

ጠቋሚ ተውላጠ ስሞች (Demonstrative  pronouns)                    

 

አገልግሎት

 

 

ምሣሌ፦

ይህ (This)

ያ (That)

እነዚህ ጠቋሚ ተውላጠ ስሞች ነጠላ ስሞችን ለመጠቆም ያገለግላሉ። ይህ እኔ የምፈልገው ዘገባ ነው።

(This is the report I want).                                    

በጣም የሚገርም ነው! (That is amazing!)                 

እነዚህ (These)

እነዚያ (Those)

ብዙ ስሞችን ለመጠቆም ያገለግላሉ። These are our children.                        እነዚህ ልጆቻችን ናቸው።

እነዚያ ቤተሰቦቻችን ናቸው። Those are our families. 

ይህ (This)

እነዚህ (These)

በቅርብ ቦታ ላይ ያለን ነገር ለመጠቆም ያገለግላሉ። እሱ ይህንን ሰጠኝ። (He gave me this.)       

እነዚህ መኪናዎቼ ናቸው። (These are my cars.)           

    (That)

    እነዚያ (Those)

በሩቅ ቦታ ወይም ጊዜ ላይ የሚገኝን ነገር ለመጠቆም ያገለግላሉ። ያንን ተመልከት። (Look at that.)                       

እነዚያ መጥፎ ቀናቶች ነበሩ። (Those were bad days.)           

መልመጃ 8፦

ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ።

  1.           ችኛዋ እኅቴ ናት።     one is my sister. A.  እነዚህ / these         ያ / That                           
  2.   ክኒኖች ጥሩ አይደሉም።      are not good pills.                                                                                               እነዚህ / these     B.  ይህ / this
  3.   እጅግ በጣም ቀጭን ወጥ ነው።       is too thin sauce.                                                                                                   ይህ / this            B.   እነዚህ / these                  
  4. ላየው የፈለኩት ስዕል      ነው።             is the picture I wanted to see.                                  እነዚያ / those        B.     ይህ / this                   
  5.     ጫማዎቼ ናቸው።         are my shoes.                                                                ይህ / this             B.    እነዚያ / those                                          

 

 

 

 

አዛማጅ ተውላጠ ስም (Relative pronoun)

አዛማጅ ተውላጠ ስም በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ያለን ስም የሚጠቅስና የሚያመለክት ነው። አዛማጅ ተውላጠ ስም ስለ አንድ ነገር መረጃ ይሰጣል። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ውስጥ የተወሰኑ አዛማጅ ተውላጠ ስሞች አሉ እነሱም እንደሚከተለው በሠንጠረዡ ውስጥ ቀርበዋል።

አዛማጅ ተውላጠ ስሞች (Relative pronouns)  

 

 

አገልግሎት

 

 

        

      ምሣሌዎች፦

ማን (Who)

 

ማንንም (Whoever

 

 

እነዚህ አዛማጅ ተውላጠ ስሞች ያልታወቀውን የድርጊቱን ባለቤት ይጠቁማሉ።

F ትናንትና የደወለችዋ ልጅ አንችን ለማግኘት መጥታለች።

F The girl who called yesterday came to see you.                                                                  በእምነትም ክህደትን የሚለውጥ ሰው ትክክለኛውን መንገድ በእርግጥ ተሳሳተ።And whoever exchanges faith for disbelief has certainly strayed from the soundness of the way.                                                          

ምን (What)      

ምንም ነገር (Whatever)           

ለነገር ያገለግላሉ። F ማድረግ ያለብህን ነገር እኛ እንነግርሀለን። We will tell you what you should do.                                                    

F ማንኛውንም የፈለግሽውን ነገር ውሰጅ። Take whatever you like.                                        

  ያ (That)       

   

በዓረፍተ ነገሩ ውስጥ ቀድሞ የተጠቀሰውን ስም ወይም ሀሳብ ለመግለፅ ያገለግላል። F እያንዳንዱ ሰው የሚከተለውን ህግ ማወቅ/ማክበር አለብህ።You have to know the rules that everyone goes by.                                                                  

F አንተ ትናንትና የሰጠኸኝን መጽሐፍ በጣም ወድጄዋለሁ። I really liked the book that you gave me yesterday.                                                            

 ማንን (Whom)         

 

    ማንንም (Whomever)

እነዚህ ተውላጠ ስሞች ድርጊት ተቀባይ ተውላጠ ስሞች ናቸው።ስለሆነም አንድ ድርጊት የተከናወነበትን  ወይም የሚከናወንበትን አካል ይጠቁማሉ። እነዚያ ለነሱ መጽሐፉን የሰጠናቸው

Those to whom we have given the Book…                                          

አንች የወደድሽውን ማንኛውንም ሰው ማግባት ትችያለሽ። You can married whomever you like.                                                    

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

   የማን (Whose)            

 

     የማንም (Whosever)

ባለቤትነትን  ያመለክታሉ።   ለሰው ወይም ለነገር ያገለግላሉ። ከእለታት አንድ ቀን ስሙ አልመንሱር የተባለ ዝነኛና ታዋቂ ዓረብ ነበር። Once upon a time there was a famous Arab, whose name was Al Mansur.                                              የምትጠቀምበት መጽሐፍ የማንም ቢሆን  በጥንቃቄ ልተይዘው ይገባል። Whosever book you use, you must take care of it.                                                  
የትኛው (Which)

 

    የትኛውንም (Whichever)

ነገርን ለማመልከት ያገለግላሉ። ለናንተ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነውን ነገር ወስኑ። Decide which one is most important to you.                                                                       የትኛውንም አንች የወደድሽውን ቀለም መምረጥ ትችያለሽ። You can choose whichever color you like.                                        
የት (Where)

     የትም (Wherever)

ቦታን ለማመልከት ያገለግላሉ።

 

እኔ ገንዘቡን ማንም በማያገኘው ቦታ ደብቄዋለሁ። I have hidden the money where no one will find it.                                                             

ቶም ሁልጊዜ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ካሜራ ይዞ ይጓዛል። Tom always carries a camera with him wherever he goes.   

መቼ (When)

  

     መቼም (Whenever)

ጊዜን ለማመልከት ይውላሉ። F I loved maths when I was in primary school.                                                                  አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለሁሒሳብ ትምህርት እወድ ነበር።

F I laugh whenever I remember it.                                                    ባስታወስኩት ቁጥር እስቃለሁ።

 

መልመጃ 9፦ በባዶ ቦታው ላይ ትክክለኛውን Relative pronoun ወይም                         አዛማጅ ተውላጠ ስም በማስገባት ዓረፍተ ነገሩን አሟሉ።

  1. I do not know he is.                                                                                                          እሱ ማን እንደሆነ አላውቅም።
  2. I have not the slightest idea  he wants.                                                                          እሱ ምን እንደሚፈልግ በፍፁም ለማወቅ አልቻልኩም።
  3. I knew he is here.                                                                                                      እሱ እዚህ እንደሆነ አውቅ ነበር።
  4. The boy to I spoke is my cousin.                                                                                ያነጋገርኩት ልጅ ያጎቴ/ ያክስቴ ልጅ ነው።
  5. The house windows are broken is for sale.                                                                                 መስኮቶቹ የተሰባበሩት ቤት የሚሸጥ ነው።
  6. I know I like best.                                                                                       የትኛውን ይበልጥ እንደምወድ እኔ አውቃለሁ።
  7. Where are the books I brought?                                                                                   ያመጣኋቸው መጽሐፍቶች የት አሉ?
  8. It is all the same day you come.                                                                                          በማንኛውም ቀን ብትመጣ ያው ነው።
  9. This is the house I used to live.                                                                          እኔ እኖርበት የነበረው ቤት ይህ ነው።
  10. She wants to live in a country it never snows.                                                                     እሷ ፈፅሞ በረዶ በማይዘንብበት አገር ውስጥ መኖር ትፈልጋለች።
  11. How can we finish you do not help us?                                                                             አንተ ሳትረዳን እንዴት ልንጨርስ እንችላለን?

Follow me on these Social Medias:

  1. YouTube: www.YouTube/PracticeAmharic
  2. website: https://PracticeAmharic.rf.gd
  3. Telegram Channel: https://t.me/LearnAmharicChannel
  4. Telegram Group: https://t.me/LearnAmharicGroup
  5. Titok: https://www.tiktok.com/@LearnAmharic
  6. Facebook Group: https://www.facebook.com/groups/learnamhariclanguage

Please help me by sharing this pdf file to others and don’t forget to subscribe my YouTube channel too. Thanks in Advance. If you want me to teach you Amharic privately, contact me on Telegram: https://t.me/KeepLearn

 

Share it Please!