Learn Amharic through reading interesting stories: Imam Ash-shafi story

Learn Amharic through reading interesting stories: Imam Ash-shafi story

የኢማሙ ሻፊዒይ የህይወት ታሪክ (ክፍል 1) Biography of Imam Shafi’i (Part 1)

Can you read Amharic well? To learn Amharic well, master the Amharic Fidel First! Fidel is very simple, doesn’t take more than one week. And I have prepaid this quiz for you. You can refine your Fidel reading ability by making this simple but effective quiz. https://easyamharic.com/amharic-fidel-quizzes/

የኢማሙ ሻፊዒይ ውልደታቸውና የዘር ሀረጋቸው (Imam Shafi’i’s birth and lineage)

Shafi’i was born in the year of the death of Imam Abu Hanifa, the leader of the Hanafi school. Imam Shafi’i was born in the month of Rajab 150 of the Hijri calendar. Or they were born on August 767 according to the European calendar. And the place was in Gaza or Palestine.

ሥማቸው አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ቢን ኢድሪስ ቢን አል-ዐባስ፣ ቢን ዑስማን፣ ቢን ሻፊዕ፣ ቢን አስ-ሳኢብ፣ ቢን ዑበይድ፣ ቢን ሀሺም፣ ቢን ዐብዲልሙጥ-ጠሊብ፣ ቢን ዐብዲመናፍ ነው።
Their names are Abu Abdullah Muhammad Bin Idris Bin Al-Abbas, Bin Usman, Bin Shafi’, Bin As-Sa’ib, Bin Ubaid, Bin Hashim, Bin Abdulmut-Talib, Bin Abdimanaf.

ዐብዱመናፍ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አራተኛ አያት ለሻፊዒይ ደግሞ ስምንተኛ አያት ናቸው። Abdumnaf is the fourth grandfather of the Prophet (peace be upon him) and the eighth grandfather of Shafi’i.

የሻፊዒይ አባት የዘር ሀረግ ቁረይሽ ውስጥ ይገባል። ሙጥ-ጠሊቢይ ናቸው። በኑ ሙጠሊብ ኢስላም ያከበረው የቁረይሽ ጎሳ ስም ነው። በጃሂሊያም ሆነ በኢስላም ውስጥ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጎን ያልተለዩ የማይረሳ ውለታ ያላቸው ህዝቦች ናቸው።

ሙስሊሞች ላይ ማዕቀብ ተጥሎባቸው፣ ከተራራው ወዲያ ታግተው የሚበሉትና የሚጠጡት ባጡ ጊዜ፣ በኑ ሙጠሊቦች ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጎሳዎች- ከበኒ ሃሺሞች- ጋር በመሆን ለፍትህ ታግለዋል። በወቅቱ አብዛኞቹ ባይሰልሙም ከርሳቸው ጋር ችግርን ተቋድሰዋል። ይህንን ውለታ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አልረሱም። እንደውም ኢስላም ውስጥ ትልቅ ቦታ ሰጧቸው። ዘካ ከማይወስዱት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤተሰቦች ውስጥ መደቧቸው።


Shafi’i’s paternal lineage goes into the Quraish. They are hot-tempered. Banu Muttalib is the name of the Quraysh tribe that Islam honored. They are a people with unforgettable merit who were not separated from the side of the Prophet (peace be upon him) in Jahiliyyah or Islam. Sanctions were imposed on Muslims and they were kidnapped beyond the mountains and deprived of food and drink. The Banu Mu’talib along with the tribes of the Prophet (peace be upon him) – the Bani Hashim – fought for justice. Even though most of them did not pray at that time, they endured problems with him. The Prophet (pbuh) did not forget this favor. They gave them a great place in Islam. He classified them among the families of the Prophet (peace be upon him) who do not take Zakah.

አስ-ሳኢብ ቢን ዑበይድን የሻፊዒይ አያቶች ውስጥ ቆጥረናቸዋል። የበድር ጊዜ ነው የሰለሙት። መልካቸው ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ይመስል ነበር ይባላል። ሻፊዕ፣ የኢማማችን ሻፊዒይ  አያት ስም ነው። በእድሜው አነስተኛ የነበረ ሶሓባ ነው። በለጋ እድሜው ሳለ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) አግኝቷል። ኢማም አል-ሐኪም በዘገቡት ሐዲስ ውስጥ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። አነስ ናቸው የዘገቡት። እንዲህ ይሉናል፡-

“አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፉስጣጥ የምትባለዋ ስፍራ ላይ ነበሩ። ከዚያም ሳኢብ ቢን ዑበይድ መጣ። ልጁ- ሻፊዕ ቢን ሳኢብ አብሮት ነበር። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጁን አዩት እና ‘ሰውየው አባቱን መምሰሉ ከእድለኝነቱ ውስጥ ነው።’ አሉ።”

አባታቸው ኢድሪስ ቢን አል-ዐባስ ናቸው። “ተባላህ” ከሚባል ቦታ የመጡ ሰው ናቸው። መዲና ውስጥ ኖረዋል። እዚያ ደስ የማያሰኛቸውን ነገር ሲያዩ ወደ ዐስቀላን አመሩ። ፊሊስጢን ማለት ነው። ህይወታቸው እስክታልፍ ድረስ እዚያው ኖሩ። የህልፈታቸው ጊዜ ሻፊዒይ ከአንቀልባ አልተላቀቁም።

ኢድሪስ ደሃ ነበሩ። እናታቸው ደግሞ- እንደ አብዛኞቹ የታሪክ ምሁሮኖች እምነት- የአዝድ ወይም የአሰድ ጎሳ ሰው ናት። ታላቅ የአምልኮ እና አላህን ፈሪ ሴት ነበረች። ንቁ ተፈጥሮ የነበራት እና አዋቂ ሴት ናት። ጥልቅ ግንዛቤዋን እና ንቃቷን የሚያመለክት አንድ ታሪክ አለ።

ታሪኩ ይህ ነው፡-

“የሻፊዒይ እናት ከአንድ ሴት እና ከአንድ ወንድ ጋር በመሆን ፍርድ ቤት ለመመስከር ሄደች። የምስክርነት ሂደቱ ላይ ዳኛው ሁለቱን ሴቶች ሊያለያይ ፈለገ። የሻፊዒይ እናት ግን እንዲህ የማድረግ መብት የለህም አለች። አላህ እንዲህ ይላል፡-

أَن تَضِلَّ إِحْدَاهُمَا فَتُذَكِّرَ إِحْدَاهُمَا الْأُخْرَىٰ

“አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታውሳት ዘንድ..” (አል-በቀራህ 2፤ 82)

ዳኛውም የርሷን ሃሳብ ወደደ። ይህች ሴት ሻፊዒይን በመገንባት ሂደት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዖ ነበራት።

ሻፊዒይ አባታቸውን በሞት ካጡ በኋላ እናታቸው ወደ መካ በመውሰድ ከአባታቸው ወገኖች- ከቁረይሾች- ጋር እንዲያድጉ አድርገዋል።

አል-ሐኪም በሰነዳቸው ሙሐመድ ቢን ዐብዱላህ ቢን አል-ሐከምን ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት አሽ-ሻ-ፊዒይ እንዲህ ብለዋል፡- “ገዛ ውስጥ ተወለድኩኝ፤ ከዚያም እናቴ ወደ ዐስቀላን ይዛኝ ሄደች።” 

አል-ባግዳዲይ በዘገቡት ሌላ ዘገባ ደግሞ ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡- “ፊሊስጢን ውስጥ በምትገኝ አል-የመን የምትሰኝ አካባቢ ላይ ተወለድኩ። ከዚያም እናቴ እንዳልባክን ሰጋች። “ወደ ቤተሰቦችህ ሂድ። እንደነርሱ ትሆናለህ። በዝምድናህ እንዳትሸነፍ እሰጋለሁ።” አለች። ከዚያም ወደ መካ ላከችኝ። ያኔ አስር አመት ገደማ ይሆነኝ ነበር። እዚያ ወደ አንድ ዘመዴ ተጠጋሁ። ዒልም መፈለግም ጀመርኩ።”

አስተውል፣ ጥሩ የዘር ሀረግ እና መልካም አስተዳደግ ሰውን ታላቅ ያደርጋሉ። ለሰዎችም ቅርብ ያደርጉታል። የሰዎችንም ስሜት በቀላሉ ይረዳል። ችግራቸውን ይካፈላል። ሻፊዒይ እንዲህ ነበሩ።

2. ገፅታቸው እና ተክለ-ሰውነታቸው

ኢብኑ ሰላሕ እንዲህ ይላሉ፡- “ሻፊዒይ ረዥም፣ አንገተ መለሎ፣ ባታቸው እና ታፋቸው የገዘፈ፣ ጠይም፣ የጎን ፂማቸው ቀለል ያለ፣ የአገጭ ፂማቸውን ሒና የሚቀቡ፣ ድመፀ-ስርቅርቅ፣ ዝምታቸው የሚያምር፣ ጭንቅላታቸው ትልቅ፣ ፊታቸው የተዋበ፣ ግርማ ሞገሳቸው የሚያስፈራ፣ አንደበተ-ርቱዕና ምላሳቸው የሚጣፍጥ ሰው ነበሩ።

ክራንቻ ጥርሳቸው ረዥም ነበር። አፍንጫቸው ላይ ጥቁር ምልክት ነበራቸው። በከንፈር እና በአገጫቸው መሀል ያለው ፂማቸው ረዥም ነበር። ጥርሳቸው ነጭና ፍንጭት ነበር።”

አል-በይሀቂይ ከዩኑስ ቢን ዐብዲል-አዕላ ይዘው የዘገቡት ዘገባ ላይ እንዲህ ተብሏል፡- “ሻፊዒይ መሀለኛ ቁመት፣ ግንባራቸው ግልጥ፣ ለስላሳ ቆዳ፣ ጠየም ያሉ፣ የጎን ፂማቸው ቀላል ነበሩ።”

አል-ሙዘኒይ የሻፊዒይን ገፅታ እንደሚከተለው ይገልፁታል፡- “እንደ ሻፊዒይ ያለ ውብ ሰው አላየሁም። ፂማቸውን ሲጨብጡት ከእጃቸው አያልፍም ነበር።”

ድምፃቸው ውብ ነበር። በህር ቢን ሰኽር እንዲህ ይገልፁታል፡- “ማልቀስ ስንፈልግ ‘ወደ ሙጠሊቢዩ ወጣት እንሂድ ቁርአን ያንብብልን።’ እንባባላለን። ወደርሱ ስንመጣ ቁርአን ያነብልናል። ሰዎች ድምፁን ሲሰሙ ራሳቸውን ስተው ይወድቁ ነበር። የድምፁ ማማር ማርኳቸው በለቅሶ ብዛት ይንጫጩ ነበር። ሰዎች እንዲህ ሲሆኑ እርሱ ማንበቡን ያቆማል።”

አሕመድ ቢን ሷሊህ እንዲህ ብለዋል፡- “ሻፊዒይ ከድምፃቸው ማማር የተነሳ ንግግራቸው ደውል ይመስላል።”

ረቢዕ ቢን ሱለይማን የሻፊዒይ አለባበስ እንዴት ነበር? ተብለው ተጠየቁ፣ “አለባበሳቸው መሀከለኛ ነበር። በጣም ውድ ልብሶችን አይለብሱም። የተልባግርና የባግዳድ ጥጥ ያዘወትሩ ነበር። ቆብ ያጠልቁ ነበር። ብዙ ጊዜ ጥምጣምና ጫማ አይለያቸውም ነበር። በግራ እጃቸው ላይ ቀለበት ያጠልቁ ነበር። ቀለበታቸው ላይ ‘ለሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ በአላህ መተማመን ብቻ ይበቃዋል።’ የሚል ፅሁፍ ተቀርፆበታል።”

3. እውቀት ፈላጊ

የአያቶቻቸው ሃገር ውስጥ ሻፊዒይ ለዒልም ዐይናቸውን መክፈት ጀመሩ። የዓለም ሙስሊሞች ልብ ማረፊያ፣ የራእዩ መውረጃ፣ የኢስላም መብቀያ የሆነችው መካ ውስጥ። ሃገሩን መላመድ ጀምረዋል። ታላቅነትንና ክብርን ያለሙ ሰው ናቸው። እንደርሳቸው ለሆነ ሰው ከዒልም ውጪ ሌላ አማራጭ አለው?!…

የሻፊዒይ እናት ምሳሌ ናት

እናታቸው ማንበብ እና መፃፍ እንዲማሩ ወደ አስተማሪ ልትወስዳቸው ፈለገች። ለመምህሩ የምትከፍለው ገንዘብ የላትም። ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡-

“ከእናቴ እንክብካቤ ሥር የምኖር የቲም ነበርኩ። እናቴ ለመምህር የምትከፍለው ገንዘብ አልነበራትም።”

እዚህ ጋር እናቶችን እንምከር። የሻፊዒይ እናት ድሃ ብትሆንም ልጇን ለማስተማር ያላትን ጉጉት ተመልከቱ። ሁላችሁም እንዲህ ልትሆኑ ይገባል። ለልጆቻችሁ የምታወርሱት አስተማማኝ ኃብት እውቀት ብቻ ነው።

አንድ ቀን መምህሩ አረፈደ። ትንሹ ልጅ ግን ህፃናትን ሰብስቦ ማስተማሩን ተያያዘው። መምህሩ ይህ ህፃን ተራ ልጅ እንዳልሆነ አወቀ። እርሱ በሚዘገይበት ሰዓት እንዲያስተምር እና የትምህርት ክፍያውን ሊተውለት ወሰነ። ሻፊዒይ ስለራሳቸው ሲተርኩ እንዲህ ይላሉ፡-

“እኔ ቁርኣንን አነብብ ነበር። አንዳንድ አንቀፆችን መምህሩ ለህፃናት ሲያስተምር እየሰማሁ እሸመድዳለሁ። አስነብቧቸው ሲያበቃ ያነበቡትን ሁሉ ሸምድጄ ጨርሻለሁ። አንድ ቀን መምህሬ ‘ካንተ ገንዘብ መቀበል አይፈቀድልኝም።’ አሉኝ።”

በዚያን ጊዜ መካ የዒልም ማዕከል ነበረች። በርካታ የሐዲስና የፊቂህ አዋቂዎች ነበሩባት። ሰባት ዓመት ሳይሞላቸው ቁርአንን በቃላቸው ይዘዋል (ሐፍዘዋል)። ከዚያም የእውቀት ማዕድ የሚዘረፍባቸውን መድረኮች በመደበኛ ተሳታፊነት መከታተል ጀመሩ። እውቀት ፍለጋ ብዙ ሀገራትን አዳረሱ።

አላህ (ሱ.ወ) ታላቅ የዕውቀት ፍቅርን ለግሷቸዋል። ጥርት ያለ የዐረብኛ ቋንቋ ችሎታና የሰላ አንደበት ይኖራቸው ዘንድ ከዓረቦች መሀል በቋንቋ ችሎታቸው የታወቁ ወደ ሆኑት የሁዘይል ጎሳዎች በተደጋጋሚ ይሄዱ ነበር።

“ከመካ ወደ ሁዘይል አመራሁ። ንግግራቸውን እና ባህላቸውን ለመማር በረሃው ላይ ሰነበትኩ። ሁዘይሎች ንግግር አዋቂዎች ናቸው። ሲጓዙ አብሬያቸው እጓዛለሁ። ሲያርፉም ያሉበት ቦታ አርፋለሁ። ወደ መካ ስመለስ ግጥሞችን መግጠም፣ የዐረቦችን ዘር መቁጠር እና ታሪክ መንገር ጀመርኩ።” ይላሉ።

ቀስት ውርወራና ጀግንነት

ሻፊዒይ ሁዘይሎች ጋር የተማሩት ቋንቋና ታሪክን ብቻ አልነበረም። ቀስት ውርወራ ተምረዋል። ለተማሪዎቻቸው የተረኩትን እናድምጥ፡- “ሁዘይሎች ጋር ትኩረቴን የሳቡት ሁለት ነገሮች ናቸው። ቀስት ውርወራ እና ዕውቀት። ቀስት ወርውሬ ከአስር አስር እመታ ነበር።” ስለዒልም ግን ሳይናገሩ ዝም ሲሉ አዳማጮቻቸው “ወላሂ እርሶ በዒልሞት ከቀስቱ የበለጡ ኖት!” አሉ።

ለቀስት ውርወራ እና ለዕውቀት የነበራቸው ትኩረት ስብእናቸው የተሟላበትን ምክንያት ያስረዳልናል። “ዘምዘም ውሃን ለሦስት ነገሮች ብዬ ጠጥቼዋለሁ። ለቀስት ውርወራ- አስር ከአስር ኢላማዬን ሳልስት እመታለሁ።… ፤ ዘምዘምን ለዒልም ጠጥቼዋለሁ። ይኸው አሁን ደግሞ ለጀነት እጠጣዋለሁ።” ይላሉ። አሁንም ለቀስት ውርወራ የነገራቸውን ፍቅር እንዲህ ይገልፁልናል። “ቀስት መወርወር አበዛ ነበር። በረሃው ላይ ብዙ ከመቆሜ የተነሳ ሐኪም ኩላሊት እንዳይዝህ ይለኝ ነበር።”

ጀግና ፈረሰኛ ናቸው። “ሻፊዒይ እጅግ የላቁ ጀግና ነበሩ። ጎበዝ ፈረሰኛም ናቸው። የራሳቸውን ጆሮ እና የፈረሱን ጆሮ ይዘው በፍጥነት ይጋልቡ ነበር።” ይላሉ፤ አል-ረቢዕ።

* * *

ኢማሙ ካደጉ በኋላ የሚጽፉአቸው ፅሁፎችና የሚያቀርቧቸው ዲስኩሮች በወቅቱ የነበሩ ምሁራንን አትኩሮት የሳበ ነበር። ዕውቀትን በመፈለግ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ጉጉት የተመለከቱት ሸይኻቸው ሙስሊም ኢብኑ ኻሊድ አል-ዛንጊ በልጅነት ጊዜያቸው ገና ከአስራ አምስት አመት ባልዘለሉበት ጊዜ ፈትዋ እንዲሰጡ ፈቀዱላቸው።

“ኢብኑ ዑየይና፣ ሙስሊም ኢብኑ ኻሊድ፣ ሰዒድ ኢብኑ ሳሊም፣ ዐብዱልመጂድ ኢብኑ ዐብዲልዓዚዝ እና የመካ ሸይኾች ባጠቃላይ ሻፊዒይን ከልጅነታቸው ጀምሮ ያውቋቸዋል። አእመሮአቸው በሳል፣ ጭምትና አስተዋይ እንደነበሩም ይመሰክራሉ። ከልጅነታቸው ጀምሮ ክፉ ነገሮች ያልተዘገቡባቸው ታላቅ ሰው እንደነበሩ ያምናሉ።”

አል-ረቢዕ ኢብኑ ሱለይማን- አገልጋያቸው፣ ተማሪያቸውና የመፅሀፎቻቸው ዘጋቢ- “የሻፊዒይ አእምሮ የምድርን ግማሽ ከሞሉ ሰዎች አእምሮ ጋር ቢመዘን ሚዛን ይደፋል። ሻፊዒይ የዚህ ዘመን ሳይሆን ያለፉት የእስራኤል ልጆች ውስጥ የነበረ ሰው ቢሆን እንኳን አሁን ያሉት ሰዎች ከርሱ ፈላጊዎች ነበሩ።” ይላሉ።

ዕውቀትን ከታላላቆች…

በሻፊዒይ የልጅነት ጊዜ የኢማሙ ማሊክ ዝና ጫፍ የዘለቀበትና አል-ሙወጣእ የሚባለው የሐዲስ ዘገባዎችን የያዘው ድርሰታቸውም ዐለምን ያዳረሰበት ዘመን ነበር። ህፃኑ ሻፊዒይ ገና የአስር ዓመት ልጅ የነበሩ ቢሆንም ወደ መዲና ሄደው ኢማሙ ማሊክን ለመገናኘት ወሰኑ። ይሁንና አል-ሙወጣእ የሚባለውን የኢማሙ ማሊክ ኪታብ ቅድሚያ በልቤ ሳልሸመድድ አልሄድም በማለት ጉዞአቸውን አዘገዩት።

ኢማሙን ለማግኘት ያደረጉት መሰናዶ አስደናቂ ነው። በየመስጂዱ ይዞራሉ። ዒልም ለመቅሰም ዑለማኦችን ያድናሉ። በታላቅ የእውቀት ፍቅር። በስል አእምሮ። ቁርአንን ከሸመደዱ በኋላ ሐዲሶችን መሸምደድ ጀመሩ። ሐዲስን ያፈቅሩ ነበር። የሐዲስ ሊቃውንት ጋር እየዞሩ የሚሰሙትን ይሸመድዳሉ። አንዳንዴ ጠጠር ላይ ይፅፉታል። አንዳንዴ ቆዳ ላይ ይመዘግቡታል። አንዳንዴ በየፍርድ ቤቱ እየዞሩ በአንድ ጎኑ ያልተፃፈበት ወረቀት ይለምናሉ። በጀርባው ሊፅፉበት። በዚህ ሁኔታ አል-ሙወጣእን ሸመደዱ።

እንግዲህ ይህ ከህፃንነት በፊት የተገኘ ወጣትነታቸው ነው። ህጻናት የሚጠመዱበት ጨዋታና ቀልድ አልደነቃቸውም። ዕውቀትን አልመው ልጅነታቸውን ለርሱው ሰዉት።

ወደ መዲና

ወደ መዲና ስላደረጉት ጉዞ አስደናቂ ታሪክ ይወራል። እራሳቸው ሻፊዒይ ይተርኩታል። እንዲህ እናቀርበዋለን፡-

“…ወደ መካ ሄድኩኝ። ገጠር ውስጥ ከሁዘይሎች ጋር ኖርኩኝ። ንግግራቸውን ተማርኩኝ። ባህላቸውን አጠናሁ። በቋንቋ ችሎታቸው የላቁ ነበሩ። እነርሱ ጋር አስራ ሰባት አመት ኖርኩኝ። ሲጓዙ አብሬያቸው፤ ሲያርፉም እያረፍኩ። ወደ መካ ስመለስ ግጥም መግጠም ጀመርኩ። የዓረቦችን ቋንቋ እና ታሪክ መንገር ጀመርኩኝ። የዙበይሪይ ጎሳ አባል የሆነ ከአጎቴ ልጆች አንዱ አገኘኝ። ‘የዐብዱላህ አባት ሆይ! ከዚህ የቋንቋ ዕውቀትህ እና የማስተዋል ችሎታህ ጋር የፊቅህ እውቀት ቢጨመር የዘመንህን ሰዎች ትልቅ ነበር!!’ አለኝ። ‘ዕውቀቱን ፍለጋ የምንፈልገው ሰው ማን ቀረ?’ አልኩት። ‘ማሊክ ቢን አነስ፤ የሙስሊሞች አይነታ፣ ዋና።’ አለ። ልቤ ውስጥ ፍላጎቱ ጨመረ። አል-ሙወጣእ የተሰኘውን መፅሀፍ መፈለግ ጀመርኩ። ከአንድ ሰው ተዋስኩት እና በጥቂት ቀናት ውስጥ በቃሌ ሸመደድኩት። ከዚያም ወደ መካ ሹም ሄድኩኝ። ወደ መዲናው አስተዳዳሪ እና ወደ ማሊክ ቢን አነስ ደብዳቤ እዲፅፍልኝ ጠየኩት። ፃፈልኝ።

መዲና ገባሁ። ደብዳቤውን ለሹሙ አደረስኩ። ካነበበው በኋላ፡- ‘ወደ ማሊክ ደጃፍ ከምደርስ ከመዲና መሀል እስከ መካ ድረስ ባዶ እግሬን ብሄድ ይቀለኛል። እርሱ ደጃፍ ጋር በመቆም መዋረድ አልሻም።’ (ኢማም ማሊክ ጋር ሹሙ የተለየ ክብር አይሰጠውም።)

አላህ አሚሩን ያብጀው። ለምን አያስልክባቸውምና እርሳቸው አይመጡም? አልኩኝ። ‘ወይ ጉድ! እኔ እና አብረውኝ ያሉት ሰዎች ሁሉ የዐቂቅ አቧራ ቢነካን እና ጉዳያችን በተሳካ!’ አለ፤ የመዲናው ሹም። (እግራችን ላይ የዐቂቅን አቧራ ሲመለከቱ ኢማሙ ካዘኑልን ማለቱ ነው።)

ከዐስር በኋላ ተቀጣጠርን። አብረን ሄድን። ወላሂ እንደተባለው ሆነ። የዐቂቅ አቧራ ነካንና እቤታቸው ደረስን። አንድ ሰው ቀደም አለና በሩን አንኳኳ። አንዲት ጥቁር ሴት ወጣች። ‘እኔ ደጃፍ ላይ እንዳለሁኝ ለአሳዳሪሽ ንገሪልኝ።’ አላት፤ አሚሩ። ወደ ውስጥ ገባችና ቆየች። ከዚያም ተመልሳ መጣችና ‘ጌታዮ ሰላምታ አቅርበዋል። ጥያቄ ልትጠይቅ ከመጣህ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፈውና መልስ ይመጣልሃል። ሐዲስ ለመስማት ፈልገህ ከሆነ መደበኛ ቀኑ መች እንደሆነ ታውቃለህ። ስለዚህ አሁን ሂድ።’ ብለውሃል፤ አለች። ከዚያም አሚሩ ‘እጄ ላይ የመካ አሚር ደብዳቤ አለ። አሳሳቢ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው በያቸው።’ አላት። ወደ ውስጥ ገባችና ወንበር ይዛ ተመለሰች። ወንበሩን አስቀመጠችው። ከዚያም ኢማም ማሊክ ከአስፈሪው ግርማቸው ጋር ብቅ አሉ። ረዥም ናቸው። ፂማቸው እርጅናቸውን ይጠቁማል። ተቀመጡ።

ሹሙ ደብዳቤውን ሰጣቸው። አነበቡት። ‘ይህ ሰው ዕውቀት ፈላጊ ነው።… ሐዲስ አስተምረው…’ የሚለው ጋር ሲደርሱ (ለሻፊዒይ ትኩረት እንዲሰጡ ትእዛዝ የሚሰጥበት ቦታ ጋር) ደብዳቤውን ጣሉት። ‘ሱብሐነላህ! የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዒልም በምልጃ ይሰጥ ጀመር እንዴ!?’ አሉ። የመዲናው ሹም ሊያናግራቸው እንዳልቻለ ተረዳሁ። ‘አላህ ያብጆት! እኔ የሙጥ-ጠሊቢይ ነኝ።’ ብዬ ስለራሴ ነገርኳቸው። ዒልም ፍለጋ የደረስኩበትን ሁሉ አስረዳኋቸው። ንግግሬን ሲሰሙ ተመለከቱኝ። ማሊክ ፊራሳ ነበራቸው። ሰዎችን በማየት ስብእናቸውን ይገምቱ ነበር። ‘ሥምህ ማን ነው?’ አሉኝ። ሙሐመድ አልኳቸው። ‘ሙሐመድ ሆይ! አላህን ፍራ። ኃጢያትን ተጠንቀቅ። አንተ ታላቅ ነገር ይኖርሃል። አላህ ልብህ ውስጥ ብርሃን አድርጓል። በኃጢያት አታጥፋው። ነገ ስትመጣ የሚያነብልህ ሰው ጋር አብረህ ትመጣለህ።’ አሉ። በጧት ወደርሳቸው ሄድኩኝና መፅሃፉ በእጄ ሁኖ በቃሌ ማንበብ ጀመርኩኝ። ማሊክን እየፈራኋቸው ንባቤን ማቆም ስፈልግ ንባቤ ማርኳቸው ‘አንተ ወጣት ሆይ ቀጥል!’ ይሉኛል። በጥቂት ቀናት ውስጥ ተምሬ ጨረስኩኝ። ከዚያም ኢማም ማሊክ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየሁ።”

ሻፊዒይ ከማሊክ ከቀሰሙት እውቀት በተጓዳኝ ከኢብራሂም ኢብኑ ሰዕድ አል-አንሷሪ፣ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ሙሐመድ አደ-ዳራወርዲ፣ ሙሐመድ ኢብኑ ሰዒድ ኢብኑ ፋዲቅ እና ከሌሎችም የመዲና ሊቃውንት እውቀትን ቀስመዋል።

4. ዳኝነት

ቆይቶም ከኢማሙ ማሊክ ሞት በኋላ ኢማሙሽ-ሻፊዒይ የነጅራን ዳኛ (ቃዲ) ተደርገው ተሾሙ። በህዝቦች መካከል ፍትህን አሰፈኑ። በፍትሃዊ አስተዳደራቸው ደስተኝነት ያልተሰማቸው የተወሰኑ ክፍሎች ኸሊፋው ሐሩን አል-ረሺድ ዘንድ ከሰሷቸው። ኸሊፋውም በ184 ዓ.ሂ/ 800 ዓ.ል እርሱ ዘንድ እንዲቀርቡ አዘዘ።

ኸሊፋው ፊት ቀርበው በተስተካከለ አንደበትና በተቀናጀ ምክንያታዊ መከራከሪያ ለራሳቸው ተከላከሉ። በሁኔታቸው የተደነቀው ኸሊፋም በነፃ ለቀቃቸው። ሃምሳ ሺህ ዲናርም ሸለማቸው። እርሳቸው ግን ከቤተ-መንግስቱ በር ሳይወጡ በስጦታ ያገኙትን ገንዘብ ለኸሊፋው አገልጋዮችና ለቤተ-መንግስቱ ዘቦች አከፋፈሉት።

5. ፊራሳ እና ሻፊዒይ

ፊራሳ ማለት ሰዎችን በመመልከት ላያቸው ላይ ከሚታዩ ምልክቶች መሰረት ስብእናቸውን የመተንተን ችሎታ ነው። ሻፊዒይ ይህን እውቀት ተክነውታል። በተግባርም ሰርተውበታል። ህፃን እያሉ በረሃው ላይ ከሁዘይሎች ጋር ሲዞሩ እውቀቱን በተግባር ቀስመውታል። ከዚያም የመን ውስጥ በዚሁ ጉዳይ ላይ የተከተቡ መፅሃፍትን አግኝተው አጥነተውታል።

በዚህ ዙርያ ከሚነገሩ አስደናቂ የሻፊዒይ ገጠመኞች አንዱን እንተርክ። አል-ሑመይዲይ የዘገቡት ነው። እራሳቸው ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ እንዲህ ይተርኩታል፡- “በፊራሳ ዙርያ የተከተቡ መፅሃፍትን ፍለጋ ወደ የመን አመራሁ። አግኝቼም ፃፍኳቸው። ከዚያም ሰብስቤ ስመለስ እቤቱ ውስጥ የተቀመጠ አንድን ሰው አገኘሁ። አይኑ ሰማያዊ ነው። ግንባሩ ወጣ ያለ ነው። ፂም የለውም። ‘ማረፊያ አገኝ ይሆን!’ አልኩት። ‘አዎን!’ አለኝ። ፊቱ ላይ መጥፎ ሰው እንደሆነ አነበብኩ። (በፊራሳ እውቀቴ ተጠቅሜ መጥፎ ሰው እንደሆነ አሰብኩኝ።) እርሱ ግን አሳረፈኝ። ቸር ሰው እንደሆነ አየሁ። እራት ሰጠኝ። ሽቶ ገዛልኝ። ለፈረሴ ቀለብ ሰጠኝ። ፍራሽ አቀረበልኝ። መጠቅለያ ሰጠኝ።

ለሊቱን ሙሉ ስገላበጥ አደርኩ። እነዚህን መፅሀፍት ምን ላድርጋቸው አልኩኝ። (የፊራሳ መፅሃፍት ምን ያደርጉልኛል። ይኸው ይህን ሰው በፊራሳዬ ስገመግም ተሳሳትኩኝ። ስለዚህ መፅሃፍቶቹ ምንም አያደርጉም አልኩኝ።) ሲነጋ ለአሽከሬ ‘ኮርቻ ጫንልኝ!’ አልኩት። እንዳልኩት አደረገ።

ከዚያም ወደ ሰውየው አለፍ ብዬ ‘መካ መጥተህ በዚ-ጡዋ በኩል ስታልፍ የሙሐመድ ቢን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይን ቤት ጠይቅ!’ አልኩት። (ውለታህን እከፍል ዘንድ ወደ እኔ ጎራ በል።)

ሰውየው ‘እኔ የአባትህ ባርያ መሰልኩህ!?’ አለኝ።

‘ምን ለማለት ፈልገህ ነው?’ አልኩት።

‘ምግቡን በሁለት ዲርሃም፣ ወጡን እንደዛው፣ ሽቶውን በሦስት ዲርሃም፣ ለፈረስህ መኖ በሁለት ዲርሃም፣ የፍራሽ እና የአንሶላ ኪራይ ሁለት ዲርሃም ክፈል!’ አለ።

አሽከሬን እንዲከፍል አዘዝኩና ‘ሌላ ይኖርብኛል ይሆን?!’ አልኩት።

‘አዎን! የቤት ኪራይ። ነፍሴን አጣብቤ ላንተ አስፋፍቼልህ የለ!’ አለ።

እነዚያ መፅሃፍትን በማጥናቴ በራሴ ላይ ቀናሁ። (ፊራሳዬ አልሳተም።) ‘ሌላስ አለብኝ!?’ አልኩት።

‘ሂድ! አላህ ያዋርድህ! እንዳንተ አይነት መጥፎ ሰው አላየሁም!’ አለኝ።”

6. ስለህክምና ይቆጫሉ

ሐርመላ እንዲህ ይላሉ፡- “ሁለት ነገሮችን ሰዎች ችላ ብለዋቸዋል። ህክምና እና የዓረብኛ ቋንቋን። ሻፊዒይ ሙስሊሞች የህክምናን ዕውቀት ችላ በማለታቸው ይበሳጩ ነበር። ‘የዒልምን አንድ ሦስተኛ ሙስሊሞች ችላ አሉት! ለአይሁድና ነሳራዎች ተዉላቸው!’ እያሉ ይቆጡ ነበር።”

ሰዎች ህክምና እንዲማሩ ይቀሰቅሱ ነበር። አል-ረቢዕ ቢን ሱለይማን እንዲህ ይላሉ፡- “ሻፊዒይ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ። ‘ዒልም ሁለት አይነት ነው። የዲን ግንዛቤ ዒልም እና የአካል ህክምና ዒልም (እውቀት)። ከዲን ትምህርቶች ሁሉ ፊቅሂ በላጩ ነው። ከዱንያ ትምህርቶች ሁሉ ደግሞ ህክምና የላቀው ነው።’ በሌላ ዘገባ ‘አንድ ሀገር ውስጥ ስትገባ ፍትሃዊ መሪ፣ ፈሳሽ ውሃና አዛኝ ሃኪም ካላገኘህ እዚያ አትኑር።’ ይሉናል ሻፊዒይ። አሁንም በሌላ ዘገባ ‘ስለዲንህ የሚነግርህ ዓሊም ወይም ስለጤንነትህ የሚነግርህ ሐኪም የሌሉበት ሃገር ውስጥ አትኑር።’ እያሉ ጥበባቸውን ያካፍሉናል።”

ተከታዩን ንግግራቸውን ሳንጠቅስ ማለፍ ከበደን። አል-ረቢዕ ቢን ሱለይማን ናቸው የዘገቡት። “ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡- ‘ሃሩን አል-ረሺድ እንዲህ አለኝ፡- ‘ሙሐመድ ሆይ! እጅግ በማለዳ ቁርስ ትበላለህ አሉ።’

‘የሙእሚኖች አሚር ሆይ! አዎን!’ አልኩኝ።

‘ለምን?’

‘የሙእሚኖች አሚር ሆይ! በአራት ምክንያቶች።’ አልኩኝ።

‘እነርሱ ማን ናቸው?’ አሉ።

‘ማለዳ ላይ ውሃው ቀዝቃዛ፣ አየሩ መልካምና ዝንቡ ያነሰ ስለሆነ እና ከሌላ ሰው ማእድ ፍላጎቴን እቆርጣለሁ።’ አልኩኝ።

‘ይህ የግጥም ቤት ይወጣዋል።’ (ትልቅ ጥበብ ነው።)

 

Share it Please!