INTRODUCTION FOR Amharic PARTS OF SPEECH / Easy Amharic

አማርኛ ሰዋስው የንግግር ክፍሎች መግቢያ (INTRODUCTION FOR Amharic PARTS OF SPEECH)

When you want to buy any item from Amazon, please use my link to buy it, because I get a small commission so you can help me with that. Thank you very much in advance

Amharic language has many words. And a all these words might classified as a Noun, Pronoun, as an Adjective, Verb, Adverb, Preposition, Conjunction or as an Interjection. Any word in a sentence can be classified into one of the eight parts of speech.

አማርኛ ቋንቋ ብዙ ቃላቶች አሉት። ሁሉም የአማርኛ ቃላቶች በ ስም (Noun)፣ በተውላጠ ስም  (Pronoun)፣ በቅጽል/ገላጭ (Adjective)፣ በግስ (Verb)፣ በተውሳከ ግስ (Adverb)፣ መስተዋድድ (Preposition)፣ በመስተፃምር (Conjunction) እና በቃለ-አጋኖ (Interjection) በስምንቱ የንግግር ክፍሎች ውስጥ ይገባሉ።

The Eight Parts of Speech in Amharic are eight different words that are arranged in one sentence to form a well-organized and complete sentence.

The Eight Parts of Speech ወይም በአማርኛው ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ተብለው የሚጠሩት ስምንት ዓይነት የተለያዩ ቃላቶች ሲሆኑ በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ተሰልፈው የተስተካከለና የተሟላ ዓረፍተ ነገርን ለመመስረት የሚያስችሉ ናቸው።   

In a sentence, someone or something performs an action. The person who performs the action is called the owner of the action, a pronoun or noun, and the action performed is called a verb. All other parts of speech in a sentence are words that provide additional information about the noun or pronoun and the action or the verb.           

በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ የሆነ ሰው ወይም የሆነ ነገር አንድን ድርጊት ይፈፅማል። ይህ ድርጊቱን የሚፈፅመው አካል የድርጊቱ ባለቤት፣ ተውላጠ ስም ወይም ስም ሲባል የተፈጸመው ድርጊት ደግሞ ግስ ይባላል። ሌሎቹ በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ የሚገኙት የቃላት ክፍሎች ስለ ስሙ ወይም ስለ ተውላጠ ስሙ እና ስለ ድርጊቱ ወይም ስለ ግሱ ተጨማሪ ማብራሪያን የሚሰጡ ቃላት ናቸው።

Knowing and understanding the eight parts of speech will help you form a correct Amharic sentence; It also allows you to easily spot and correct any mistakes in any part of the sentence.                 

ስምንቱን የንግግር ክፍሎች በደንብ ለይቶ ማወቅና መረዳት ትክክለኛ የሆነ ዓረፍተ ነገር ለመመስረት ይረዳል፤ እንዲሁም በማንኛውም የዓረፍተ ነገር ክፍል ውስጥ ያለን ስህተት በቀላሉ ነቅሶ ለማውጣትና ለማረም ያስችላል።

Next, we will explore the eight parts of speech in a nutshell. ቀጥለን ስምንቱን የንግግር ክፍሎች በወፍ በረር እንቃኛለን።

 ስም (Noun)

 ስም ምንድን ነው? (What is a noun?)

ስም ወይም Noun ለማንኛውም ለማንኛውም ነገር መጠሪያነት የምንሰይመው ነገር ነው። ስም ለሰው፣ ለቦታ፣ ለነገር፣ ለረቂቅ ፅንሰ ሐሳብ (abstract idea) ወዘተ መጠሪያነት ይውላል። አሁን በተቀመጥንበት ዙሪያ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ እነዚያ ሁሉም ስም አላቸው። ለምሣሌ፦

  • ፈጣሪ /አምላክ (God Almighty)
  • ቅዱስ መጽሐፍት (Holy Book)
  • እናት (Mother)
  • አባት (Father)
  • ሰዎች (People)
  • አልጋ (Bed)
  • ብርድ ልብስ (Blanket)
  • ወንበር (Chair)
  • መስታወት (Mirror)
  • አምፖል (Pulp)
  • ደርደሪያ (Shelf)
  • ገበያ (Market)
  • የመሬት ስበት (Gravity)
  • ድንጋይ (Stone)
  • ጥናት (Research) ወዘተ… (etc…)

     ምሳሌ በዓረፍተ ነገር ውስጥ:- Example in a sentence: The words in red in the sentences below are nouns.

  • ሌባሙሉ አሁን ካሁን ተያዝኩኝ እያለ በፍርሃት ሲበረግግ ዋለ። The thief passed the day in fear of discovery.
  • አበበ በጣም ፈሪ ሰው ስለሆነ ሁል ጊዜ ይጨነቃል። Abebe is a very timid person and is always worried.
  • አሕመድና ሑሰይን ቃሬዛውን በጥንቃቄ አነሱት። Ahmed and Hussein lifted the stretcher

ከላይ በቀረቡት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ያሉት ሌባ (thief) ቀን (day) ፍርሃት (fear) ሰው (person) አበበ (Abebe) ጊዜ (time)፣ አሕመድ (Ahmed)፣ ሑሰይን (Hussein) ቃሬዛ (stretcher) የሚሉት ቃላቶች ስሞች ናቸው።

A noun can be singular or plural. Usually, we add the suffix “ዎች” to the end of names to make them plural, and sometimes we change the last letter to the seventh letter and add the Amharic letter “ች”. For example:

           ነጠላ ስሞች፡       ብዙ ስሞች
የስፖርት ሜዳ (Stadium) የስፖርት ሜዳዎች (Stadiums) 
ገበያ (Market) ገበያዎች (Markets)                                                 
ድንጋይ (Stone) ድንጋዮች (Stones)
ጥናት (Research) ጥናቶች (Researches)                                                  
ጣዖት god ጣዖቶች (gods)  

ለምሳሌ ከላይ እንዳየነው፣ ስም ነጠላ (Singular) እና ብዙ (Plural) ሊሆን ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ ስሞችን ወደ ብዙ ለመቀየር መጨረሻ ላይ ዎች የሚል ቅጥያ እንጨምራለን፣ አንዳንዴ ደግሞ መጨረሻ ላይ ያለውን ፊደል ወደ ሰባተኛ ፊደል ከቀየርነው በኋላ “ች” የምትለዋን የአማርኛ ፊደል እንጨምርበታለን ከዚያ ብዙ ይሆናል።

Also, if the letter “ /of” is inserted before the name, then that name indicates the ownership of someone or something. እንዲሁም የአማርኛውን ስም ቀድሞትየሚለው ፊደል ከገባ፣ ባለቤትነትን አመልካች ስም ሊሆን ይችላል። For example:

  • ፈጣሪ ምህረት (God’s mercy)
  • ሙሐመድ ድል (Muhammed’s victory)
  • እናቶች ፍቅር (Mother’s Love)

ተውላጠ ስም (Pronoun)

ተውላጠ ስም ምንድን ነው? (What is a pronoun?)

Pronoun is a part of speech which takes the place of a noun and performs the function of a noun. ተውላጠ ስም ማለት በስም ቦታ እየገባ የስምን ተግባር የሚያከናውን የቃል ክፍል ነው። The pronouns that usually enter in the place of a noun are presented as follows:

የአማርኛ ተውላጠ ስሞች የእንግሊዝኛ ተውላጠ ስሞች
እኔ I
እኛ We
አንተ You (for male)
አንች You (for female)
እናንተ You (for plural)
እሱ He
እሷ She
እነሱ They
እንትን It

ምሳሌ፦

  • እሱ በጣም ፈሪ ሰው ስለሆነ ሁል ጊዜ ይጨነቃል። (He is a very timid person and is always worried.)
  • እነሱ ቃሬዛውን በጥንቃቄ አነሱት። (They lifted the stretcher carefully.)

The word “Abebe” is here replaced by the pronoun “እሱ” or (He) and አሕመድና ሑሰይን (Ahmed and Hussein) also replaced by the pronoun “እነሱ (they)” in the above. That is why we say “Pronoun is a part of speech which takes the place of a noun and performs the function of a noun.”

ገላጭ / ቅጽል (Adjective)

  ቅጽል ምንድን ነው? (What is an adjective?)

An adjective is a part of speech that gives additional information about a person, thing, noun or pronoun. Adjectives are words we use to describe the color, quantity, shape, size or type of something or someone.

ቅጽል ወይም Adjective ስለ አንድ ነገር ስም እና ስለተውላጠ ስሙ ተጨማሪ ማብራሪያን የሚሰጥ የቃል ክፍል ነው። የአንድን ነገር ቀለም፣ ብዛት፣ ትልቀት፣ አይነት፣ ቅርጽ ለመግለጽ የምንጠቀምባቸው ቃላት ቅጽል ወይም ገላጭ ቃላት ይባላሉ።ለምሳሌ፦

  • ቤቱ ትንሽ ናት። His house is small. (እዚህ ጋ ቤቷ ምን እንደምታክል የሚገልፀው “ትንሽ / small” የሚለው ገላጭ ወይም ቅጽል ነው።)
  • ሚስቱ ምርጥ ጸባይ አላት። His wife has the best (የሚስቱን ጸባይ የሚገልጸው “ምርጥ” የሚለው ቃል ነው። /The word “ምርጥ / the best” describes my wife’s character or her personality.

ሌባ ሙሉ አሁን ካሁን ተያዝኩኝ እያለ በፍርሃት ሲበረግግ ዋለ። The thief passed the day in fear of discovery. Here, the word “ሌባ (the thief)” is an adjective. The fidel ው” also indicates “the.”

Adjective describes the number and size of nouns and pronouns. ቅጽል ወይም Adjective የስምን እና የተውላጠ ስምን ዓይነት ብዛትና መጠን ይገልፃል። ምሣሌ፦

  • አንድ ትልቅ ጥቁር ድመት (A big black cat)
  • ትንሽ መንደር (Small Village)
  • ጠቢብ ሰው (Wise Man)
  • ህጻን ልጅ (Young Child)
  • አሮጌ ቀሚስ (Old Dress)
  • አንድ አስቀያሚ ሾፌር (Un ugly)
  • ወጣት (Young)
  • አሮጊት (Old woman)

These words in red are adjectives that describe nouns and pronouns. እነዚህ ቀይ የተቀቡት ቃላቶች ስምንና ተውላጠ ስሞችን የሚገልፁ ገላጮች ናቸው።

ግስ (Verb)

ግስ ምንድን ነው? (What is a verb?)

A verb is a word that indicates an action. The main function of verbs is to indicate an action in a sentence. The word “indicates” we just used here is also a verb. A verb indicates “to be” too. Some verbs are presented below:

ግስ (Verb) ድርጊትን አመልካች ቃል ነው። የግሶች ዋና ተግባርም በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ያለን ድርጊት ማመልከት ነው፤ አሁን እዚህ የተጠቀምነው “ማመልከት” የሚለው ቃል ራሱ ግስ ነው። እንድሁም ግስ “መሆንን” ያመለክታል። የተወሰኑ ግሶች እንደሚከተለው ቀርበዋል:-

ሮጥ To Run
ንበብ To Read
ብላት To Eat
ጠጣት To Drink
ጫወት to Play
መሆንን የሚያመለክቱ ግሶች (The verbs that indicate “to be”)
ነኝ Am
ነን/ ነህ/ ናችሁ/ ናቸው Are
ነው/ /ናት   Is

ነበርኩ/ነበረ/ች)

Was
ነበርን/ነበርክ/ሽ/ነበሩ Were

 የተሰመረባቸው ቃላቶች ግሶች ናቸው።

  • እሱ በጣም ፈሪ ሰው ስለሆነ ሁል ጊዜ ይጨነቃል። He is always worried because he is a very timid person.
  • ቃሬዛውን በጥንቃቄ አነሱት። (They lifted the stretcher carefully.)
  • That is why said verbs indicate “actions” and “to be”.

ተውሳከ ግስ (Adverb)

 ተውሳከ ግስ ምንድን ነው? (What is an Adverb?)

ተውሳከ ግስ አንድ ድርጊት እንዴት፣ መቼ እና የት እንደተፈጸመ በመግለጽ ተጨማሪ ማብራሪያን የሚሰጥ አንዱ የንግግር ክፍል ነው።

An adverb is a part of speech that provides additional explanation by describing how, when, and where an action occurred.

ልክ ቅጽል፣ ስምን እና ተውላጠ ስምን እንደሚገለጸው ሁሉ ተውሳከ ግስም ግስን፣ ቅጽልን እና ሌላ ተውሳከ ግስን ይገልጻል። ቀጥለው የቀረቡት ቃላቶች ተውሳከ ግሶች ናቸው።

መጨረሻ Finally
ተጨማሪ Additionally
ፍጥነት Quickly
ዝግታ Slowly
ጥንቃቄ Carefully
ጥብቅ Firmly
በመጨረሻ  
በመጀመሪያ  
በምሽት  
በጧት Early

 Example in a sentence: The red words are adverbs.

  • እሱ በጣም ፈሪ ሰው ስለሆነ ሁልጊዜ ይጨነቃል። He is always worried because he is a very timid person.
  • ቃሬዛውን በጥንቃቄ አነሱት። They lifted the stretcher carefully.
  • እቃህን በግደለሽነት አታዝረክርክ። Do not throw your things down so carelessly.
ሁል ጊዜ Always
በጥንቃቄ Carefully
በግደለሽነት Carelessly

  መስተዋድድ (Preposition)

 መስተዋድድ ምንድን ነው? (What is a Preposition?)

መስተዋድዶች ወይም Prepositions point out the direction of things. The next words are Prepositions.

መስተዋድዶች ወይም Prepositions ነገራቶች ያሉበትን አቅጣጫ ይጠቁማሉ። ቀጥለው የቀረቡት ቃላቶች Prepositions (መስተዋድዶች) ናቸው።

በ…ላይ on
to
ወደውስጥ into
በ…ውስጥ in
ከ…ጎን besides

 ማንቆርቆሪያው ጠረንጴዛው ላይ ነው። (The kettle is on the table.) እነዚህ ፊደላትና ቃላት አብዛኛውን ጊዜ የዋናው ቃል ላይ እየተለጠፉ አገልግሎት ላይ ይውላሉ።

 መስተፃምር / አያያዥ ቃል (Conjunction)

 መስተፃምር ምንድን ነው? (What is a Conjunction?)

መስተፃምር ወይም Conjunction is used to join two words, two phrases or two sentences together. Some of the connecting words or phrases are presented as follows:

Conjunction ወይም መስተፃምር ሁለት ቃላቶችን፣ ሁለት ሀረጎችን ወይንም ሁለት ዓረፍተ ነገሮችን በአንድ ላይ ለማጣመር ያገለግላል። የተወሰኑት አያያዥ ቃላት ወይም መስተፃምሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

እና And
(ነገር) ግን but
ስለ for
ወይም or
አይደለም Nor
ስለዚህ so
ሆኖም yet
ስለሆነ/ምክንያቱም Because
ከሆነ if
እንደሆነ whether
ካልሆነ Unless
እንደ As
ስለሆነ Since
ሳለ While

Examples in sentences:

  • እኛ ቀን እና ሌሊት ተጓዝን። We traveled day and
  • እሱ በጣም ፈሪ ሰው ስለሆነ ሁልጊዜ ይጨነቃል። He is always worried because he is a very timid person.
  • ትንሽ መጫወት ፈልጌ ነበር ግን ስራ አለብኝ። (I wanted to play a little but I have work to do.)
  • ምግብ መስራት እና ሳሀን ማጠብ ደስ አይለኝም። I don’t enjoy cooking and washing dishes.

 አንክሮ / ቃለአጋኖ (Interjection)

 አንክሮ / ቃለ-አጋኖምንድን ነው? (What is an interjection?)

Interjection ወይም ቃለ-አጋኖ / አንክሮ ሐሳብን በአጽንኦት ወይም በአንክሮ ለመግለጽ የሚያገለግል የቃል ክፍል ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜም ከቃሉ መጨረሻ ላይ የ “Exclamation mark” ወይም የ“ትእምርተ አንክሮ” ምልክትን ያስከትላል። ምሣሌ፦

  • ጉድ 
  • ጉድ ነው
  • የማይሰማ ጉድ የለም!
  • ነይ ጉዲሽን ስሚ!
  • ይገርማል። 
  • ወይ ጉድ፣ ምን ተፈጠረ ደግሞ? (እነዚህን አገላለፆች የምንጠቀመው ያልጠበቅነው ነገር ሲከሰት ነው።)
  • “እናንተ አማኞች ሆይ! የሸይጧንን ዱካ / እርምጃ አትከተሉ።” (“Oh You Who Believe! Do not follow the satan’s footstep.”) Quran (An-Nur 24: 21)
  • በፈጣሪ ስም! Oh my God!
  • ተመልከት! / ኧረ እያየህ! Look out! (ተመልከት!/ኧረ እያየህ!)
  • ዱካ

 ስርኣተነጥቦች (Punctuations)

 ስርአተ ነጥቦች ሃሳብን ግልፅ በሆነ መልኩ ለማስተላለፍ ይረዳሉ። ሀሳባችንን በተለይ በፅሁፍ በምንገልፅበት ጊዜ በተሳካ ሁኔታ እንገልጸው ዘንድ ስርአተ ነጥቦችን በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል። በፅሁፍ የምንገልጸው ሀሳብ፣ ጥያቄ፣ ትእዛዝ ወይም አድናቆት መሆኑን የምንለየው በስርአተ ነጥቦች ነው።

Punctuations help to convey ideas clearly. In order to successfully express our thoughts, especially when we express them in writing, we need to use punctuation marks properly. We use punctuations to determine whether we are expressing an idea, a question, a command, or an appreciation.

ሁሉም የዓረፍተ ነገር ክፍሎች መጨረሻቸው ላይ ስርአተ-ነጥብ ያስፈልጋቸዋል። ይህም ስርአተ-ነጥብ አራት ነጥብ (four dots) (።) ጥያቄ ምልክት (Question mark) (?) ወይም የትእምርተ አንክሮ ምልክት (Exclamation mark) (!) ሊሆን ይችላል።

All sentences need punctuation at the end. This can be four dots, (።) a question mark (?) or an exclamation mark (!).

ስለዚህ፣ Knowing the punctuation marks well is useful for understanding the Amharic language.

  • In the Amharic language there is no Capital letter and small letter. አብዛኛውን ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውሉት ሥርዓተ – ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው:-

The most commonly used Amharic punctuations are as follows:

ስርኣተነጥቦች Punctuations   Punctuation ምልክቶች
አራት ነጥብ Full stop .
ጥያቄ ምልክት ? Question mark ?
ትእምርተ አንክሮ (ቃለ አጋኖ) ! Exclamation mark !
ነጠላ ሰረዝ ፣ / ፥ Comma ,
ድርብ ሠረዝ Semi-colon ;
ሁለት ነጥብ : Colon :
ንድ ነጥብ . Dot .
ትእምርተ ጥቅስ “ ” Quotation marks “ ”
እዝባር / ወ/ሮ Slash /
    ቅንፍ ( ) ወይም Bracket ( )
  :- Colon dash :-

 መልመጃ 1፦ ቀጥለው ቀረቡት ስምንት ጥያቄዎውስጥ ስምንቱም የንግግር ክፍሎች ተካተዋል። ቃላቶች ከስምንቱ የንግግር ክፍሎች ውስጥ በየትኛው የንግግር ክፍል ውስጥ መደቡ እንደሚችሉ በመለየት፣ በተዘጋጀው የመልስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ በማስቀመጥ ተለማመዱ

  1. ለተጨማሪ ስራ ተጨማሪ ክፍያ እጠይቃለሁ። I want extra pay for extra work.
  2. አንድ ትርፍ እስኪርቢቶ አለህ? Do you have an extra pen?
  3. ዱባይ ውስጥ ብዙ ረጃጅም ህንፃዎች አሉ። There are many high buildings in Dubay.
  4. እኔ በዓለም ላይ ደስተኛና ጤነኛ ሴት ነኝ። I am happy and healthy woman in the world.
  5. የምስራች! ተጨማሪ የገንዘብ ክፍያ ልናገኝ ነውHurrah! we are getting extra pay.
  6. ስለ ሱ በአድናቆት ተናገረ። He spoke highly of him.
  7. ፈጣን መኪና በፍጥነት ይበራል። ነገር ግን ዘለቄታ የለውም። A fast car goes fast, but it does not long lasting.
  8. እነሱ የሚኖሩት ከሐይቁ በላይ ባለች ትንሽዬ ጎጆ ውስጥ ነው። They live in a small cottage above the lake.

የመልስጫ ሳጥን (አንድ ምሳሌ ተሰርቷል።)

ስም (Noun)
1.    ስራ (work) ክፍያ (pay)
2.    እስኪርቢቶ (pen)
3.    ዱባይ (Dubay) ህንፃዎች (buildings)
4.    ዓለም (world) ሴት (woman)
5.    ገንዘብ (money) ክፍያ (pay)
6.     
7.    መኪና (car)
8.    ሐይቅ (lake) ጎጆ (cottage)
ተውላጠ ስም (Pronoun)
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      
ቅጽል (Adjective)
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      
ግስ (Verb)
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      
ተውሳከ ግስ (Adverb)      
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      
መስተዋድድ (Preposition)
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      
መስተፃምር (Conjunction)
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      
ቃለ- አጋኖ (Interjection)
1.      
2.      
3.      
4.      
5.      
6.      
7.      
8.      

If you want to buy an Amharic textbook from Amazon, please buy it using this link, because I get a small commission, so you can help me with that. Thank you very much in advance.

ከአማዞን ላይ የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ መግዛት ከፈለጋችሁ፣ ይሄን የኔን ሊንክ በመጠቀም ግዙ፣ ምክንያቱም እኔ ትንሽ ኮሚሽን ስለማገኝ በዛ ልትረዱኝ ትችላላችሁ። ከወድሁ በጣም አመሰግናለሁ።

Share it Please!