Daily routines in Amharic language

Daily routines in Amharic language

የኔን የለት ከእለት እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ ዴሊ ሩቲናችሁን በአማርኛ እንደት እንደምትገልጹት ላሳያችሁ፦ Let me show you how to describe your daily routine in Amharic based on my daily activities:

Daily Routines in the amharic language
  1. ጠዋት 11 ሰአት ላይ ከመኝታየ እነሳለሁ፣ ከዚያ ሽንት ቤት እገባለሁ። ከዚያ እጄን፣ ፊቴንና እግሬን ታጥቤ መስጅድ እሄዳእሁ። I wake up from bed at 11 o’clock in the morning, then I go to the bathroom. Then I wash my hands, face and feet and go to the Mesjid.
  2. ከመስጅድ እንደተመለስኩ ኮምፒውተር እጠቀማለሁ፣ ከዚያ 1 ሰአት ላይ ቁርሴን እበላ እና ወደ ስራ እሄዳለሁ።
  3. As soon as I come back from the mosque, I use the computer, then at 1 o’clock I have my breakfast and go to work.
  4. ምሳ ሰአት ላይ ወይም 6፡15 አካባቢ አሁንም ሽንት ቤት ተጠቅሜና ተጣጥቤ ወደ መስጅድ እሄዳለሁ። At lunchtime or around 6:15, again I go to the bathroom and wash up and go to the Mesjid.
  5. ከፀሎት ተመልሼ እቤቴ እሄድና ምሳየን እበላለሁ። ከዚያ አሁንም ወደ ስራ እሄዳለሁ። I return from prayer and go home and have lunch. Then I still go to work.
  6. እንደገና 9፡30 ላይ መስጅድ እሄድና ሰግጄ አሁንም ወደ ስራ እመለሳለሁ። Again at 9:30 I go to the mosque, pray and then go back to work.
  7. ስራ እስከ 12 ሰአት ከሰራሁ በኋላ እንደገና ወደ መስጅድ እሄድና እጸልያለሁ። ከዚያ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ። After I work till 12 o’clock, I go to the mosque again and pray. Then I go home.
  8. ድጋሜ ከምሽቱ 1፡30 ሲሆን ወደ መስጅድ እሄድና እሰግዳለሁ። I go to the mosque again at 1:30 pm and pray.
  9. ከዚያ ወደቤት ተመልሼ ራቴን እበላለሁ፣ ትንሽ ቆይቼ ሶስት ሰአት ገደማ ላይ እተኛለሁ። በማግስቱ ጠዋትም የማደርገው ይህንኑ ነው። Then I come back home and have my dinner, then go to bed a little later at about three o’clock. This is what I do in the next morning too.

ምግብ የምበላው በቀን ሶስት ጊዜ ሲሆን፣ I eat three times a day.

ከጠዋቱ 1 ሰአት ከ20 አካባቢ ቁርሴን እበላለሁ I eat my breakfast around 1:20 in the morning

ከቀኑ 7 ከ 15 አካባቢ ምሳየን እበላለሁ
I eat lunch at around quarter past 7.

ከምሽቱ 2 ሰአት ከ ሩብ አካባቢ ራቴን እበላለሁ
I eat my dinner at a quarter past 2 in the evening.

ከምሽቱ 3 ሰአት አካባቢ እተኛለሁ።
I go to bed around 3pm.

ሶላት ለመስገድ ወደ መስጅድ የምሄደው I go to the mosque to pray

ከጧቱ 11 ሰአት ላይ፣ At 11 o’clock in the morning,

ከቀኑ 6 ሰአት 30 ላይ
At 6:30 p.m

ከሰአት 9 ሰአት ከተኩል ላይ፣ in the afternoon 9:30 p.m.

ከምሽቱ 12 ሰአት ከሩብ ላይ At quarter to 12 o’clock in the evening

እና ከምሽቱ 1 ሰአት ከተኩል ላይ ነው ወደ መስጅድ የምሄደው። And at 1:30 in the evening, I go to the mosque.

ቁርሴን ከጧቱ 1 ሰአት ከሩብ ገደማ እበላለሁ I eat my breakfast at about a quarter past 1 in the morning

ምሳዬን ከቀኑ 7 ሰአት ከሩብ ገደማ እበላለሁ I eat my lunch at a quarter to 7 o’clock

ራቴን ከምሽቱ 2 ሰአት ተኩል ገደማ እበላለሁ I eat my dinner at about 2:30 pm

Share it Please!