ነፃ ንግግር (Free Talk)
Greetings:
ሰላም ሊቢ፣ እንዴት ነሽ?
እናትሽ እንዴት ናት አሁን?
ተሽሏታል?
ተሻላት?
Answers:
ተሽሏታል።
አሁን በጣም ደህና ናት።
ስለ ቋንቋ፦
እኔ ፖርቹጋልኛ መናገር እችላለሁ። ትንሽ ትንሽ እስኞል ስፓኒሽኛ እናገራለሁ።
ፈረንሳይኛስ?
ፈረንሳይኛ አላውቅም።
ጀርመንኛስ?
ጀርመንኛም አላውቅም።
አልፎ አልፎ ለስራ ወደ ጀርመን እሄዳለሁ።
በቀጣይ አመት ወደ ኢትዮጵያ እመጣለሁ።
ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ስንት ብር ነው የምትከፍሉት?
አንድ ሺ ሁለት መቶ ዶላር ነው የምንከፍለው።
1200 ዶላር?
አዎ።
ኦ፣ በጣም ብዙ ነው።
በረራው ቀጥታ ነው ወይስ ትራንዚት ነው?
ቀጥታ ነው
ከዋሽንግተን ዲስ ቱ አዲስ አበባ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት አመት ቆየሽ?
አንድ አመት።
ህዝቡ ይመቻል?
አዎ፣ ይመቻል።
እዚህ ቤት ገዝታችኋል?
አዲስ አበባ?
አይ፣ አልገዛንም። አዲስ አበባ ቤት በጣም ውድ ነው። ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚሸጥበትና አዲስ አበባ ውስጥ የሚሸጥበት የቤት ዋጋ ተመሳሳይ ነው።
አዎ፣ ዲስ አበባ ውስጥ ቤት በጣም ውድ ነው።
በዚህ ሳምንት በጣም ቢዚ ነበርኩ።
ባልሽ እንዴት ነው?
ደህና ነው።
ስራ እየሰራ ነው?
ዛሬ አይሰራም።
ዛሬ ስራ የለውም።
አሁን እሱ ቁርስ እየበላ ነው።
አሁን እሱ ቁርሱን እየበላ ነው።
ን indicates an object noun, but only when we add it on a noun.
ትናትና ምን ሰራሽ?
ትናትና ስራ ሰራው። ትናንትና ብዙ ስብሰባ ነበረን።
ይሄን ሳምንት ብዙ ስራ ነበረኝ።
ስለ ሶፍትዌር ወይም መተግበሪያ እየተማርን ነው።
ወሩን ሙሉ ልምምድ አለኝ።
ወሩን ሙሉ እለማመዳለሁ።
ሶፍትዌሩን ወይም መተግበሪያውን እንደት መጠቀም እንዳለብኝ ወሩን ሙሉ እለማመዳለሁ።
ወርክደይ?
እኔም መጠቀም እችላለሁ።
ነፃ ነው?
ነፃ አይለደም።
በክፍያ ነው።
መግዛት አለብህ።
ዋጋው ስንት ነው?
እኔ እንጃ።
Other ways to say I don’t know in Amharic:
እርግጠኛ አይደለሁም። ግን ቅርብ ነው።
እኔም እስከማየው ጓጉቻለሁ።
በጣም ደህና ናት።
ያለእረፍት እየሰራች ነው።
አይዞሽ እላታለሁ።
ስንት ቀን ቀረው?
ስንት ቀን ቀራት?
ስንት ቀን ቀራቸው?
መቅረት = to be absent or to remain
ስንት ብር ቀረህ?
ስንት ቀን ቀረው?
እቀራለሁ
እንቀራለን
ትቀራለህ
ትቀሪያለሽ
ጥያቄ አለኝ።
ይመስለኛል።
ወርክደይ ውድ ይመስለኛል።
አለብኝ። I have to.
ያስፈልገኛል። I need.
መሄድ አለብኝ። I have to go.
መምጣት አለብኝ።
መማር አለብኝ።
መግዛት አለብኝ።
መግዛት አለብህ።
መግዛት አለብሽ።
መግዛት አለባችሁ።
መግዛት አለብን።
እሱ መግዛት አለበት።
መግዛት አለባት
መግዛት አለባቸው = they have to buy.
in the past
ነበረብኝ። = I had to.
ገበያ መሄድ ነበረብኝ።
አማርኛ መማር ነበረብኝ።
ላንተ መናገር/መንገር ነበረብኝ።
ላንተ መደወል ነበረብኝ።
ለኔ መደወል ነበረብህ።
ለኔ መደወል ነበረብሽ።
እንችላለን። we can.
ማስፈለግ = to be needed
አሁን = now
ባለፈው = In the past, previously

ውሀ ያስፈልገናል።
አያስፈልግም = He/it is not needed.
አስፈላጊ = Necessary
አላስፈላጊ = Unnecessary
መጮኽ አያስፈልግም። = There’s no need to shout.
መናደድ አያስፈልግም።
መሄድ አያስፈልግም።
ማሰብ አያስፈልግም።
መጨነቅ አያስፈልግም።
ማሰብ አለብህ። you have to think.
አረብኛ እየተማርክ ነው?
አልፎ አልፎ እየተማርኩ ነው።
አረብኛ ታወራለህ? ትናገራህ? ትችላለህ?
አረብኛ አውርተሃል? ተናግረሀል? ችለሀል?
አረብኛ ተምረሃል?
ብዙ አልተማርኩም።
ማውራት አልችልም።
ማንበብ ትንሽ ትንሽ እችላለሁ።
ተምሪያለሁ
ስንት ቀን ተማርሽ?
አስር አመት አለፈው
ከአስር አመት በፊት ነው። ረጅም ጊዜ ነው። እረሳሁት።
ማንበብ ችለሽ ነበር?
አረብኛ ስንት ሆሄያት አሉት?
አሁን ረስቸዋለሁ። ረሳሁት።
መርሳት = to forget
ትክክል ነሽ፣ ተመሳሳይ ናቸው።
ሂ / ከስራ ሊ ሚ ሲ ሠ
ሂብሩ ታውቂያለሽ?
አላቅም / አላውቅም።
አቃለሁ።
ከሴሚቲክ ቋንቋ ውስጥ አማርኛ ብቻ ነው የማውቀው
Negative verbs start with አ.
- አያስፈልገንም
- አልመጣም
- አላየሁም
- አልሰማሁም
- አላሰብኩም
ያስፈልገኛል። I need.
አማርኛ መማር ያስፈልገኛል።
አስፈልጎኛል = ቡና አስፈልጎኛል።
ገንዘብ በጣም አስፈልጎኛል።
ቡና እፈልጋለሁ።