Amharic Conversations
Airport Dialogue in Amharic
Airport Dialogue in Amharic
- እንደት አደሩ? Good morning.
- እንደት አደሩ፣ እመቤት? Good morning, madam.
- ተመዝግቤ መግባት ፈልጌ ነበር። I would like to check in.
- ወደ ኒው ዮርክ ነው የምበረው። I am flying to New York.
- ፓስፖርትዎን እና ትኬትዎን ማየት እችላለሁ? May I see your passport and your ticket, madam?
- በሚገባ፣ ትኬት እና ፓስፖርቴ ይሄው። Sure, here is my ticket and passport.
- ስንት ሻንጣ ነው የሚያስገቡት? How many bags are you checking in?
- አንድ ትልቅ ሻንጣ ብቻ ነው ያለኝ። I have just one big bag.
- እባክዎ ሻንጣዎን ሚዛኑ ላይ ያስቀምጡት። Please put your bag on the scale.
- በጣም ጥሩ። ሻንጣው በተፈቀደው የክብደት ልክ ነው። Perfect! Your bag is within the weight limit.
- አመሰግናለሁ። ከየትኛው በር እንደሚነሳ እና መሳፈሪያው በስንት ሰአት እንደሚጀምር ሊነግሩኝ ይላችሉ? Thank you. Can you tell me which gate I am departing from and what time the boarding starts?
- ከ 23ተኛው የመጠበቂያ ክፍል ነው የሚወጡት። የሚሳፈሩትም ከጧቱ 8፡30 ጀምሮ ነው። You are departing from gate 23 and boarding starts at 8:30 a.m.
- በረራው በሰዓቱ ስለሚነሳ ቢያንስ 30 ደቂቃ ቀደም ብለው የመሳፈሪያ ቦታው ላይ ቢገኙ ጥሩ ነው። The flight is on time so I recommend being at the gate at least 30 minutes before boarding.
- በጣም ጥሩ። ወደ ኒው ዮርክ የሚደረገው በረራ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? That’s great. How long is the flight to New York?
- ወደ ኒው ዮርክ የሚደረገው በረራ በግምት 17 ሰዓታት ይፈጃል። For the flight time to New York is approximately 17 hours.
- በሃገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5፡00 ሰአት ላይ ኒውዮርክ ይደርሳል። You should arrive in New York at around 5:00 p.m local time.
- ለመረጃው አመሰግናለሁ፣ ከዚህ በፊት በርሬ አላውቅም። ይህ የመጀመሪያው በረራዬ ነው። Thank you for the information this is my first flight I have never flown before.
- ሌላ ማወቅ ያለብኝ ነገር አለ? Is there anything else I need to know.
- በእጅዎ የሚይዙት ሻንጣ ከራስጌው ባለው የእቃ ማስቀመጫ ውስጥ ወይም ከፊት ለፊትዎ ባለው ወንበር ስር መግባት የሚችል መሆኑን ያረጋግጡ። Just make sure your carry-on suitcase fits in the overhead bin or under the seat in front of you.
- በጣም አመሰግናለሁ። መልካም ቀን! Thank you very much have a good day.
- ምስጋናዎን ተቀብያለሁ። ደህንነቱ የተጠበቀና አስደሳች ጉዞ ይሁንልዎ! You’re welcome have a safe and pleasant journey!
ወደ በረራ = Departure
እንደምን አደሩ እመቤት! እባክዎን ሁሉንም የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችዎን፣ ቀበቶዎን እና ጫማዎን እዚያ ካሉት ማስቀመጫዎች በአንዱ ውስጥ ያስቀምጡ እና ለፍተሻ በማጓጓዣ ቀበቶው ላይ ያስቀምጡ።
Good morning, madam. Please place all of your electronic devices, your belt, and your shoes in one of the bins over there, and then place them on the conveyor belt for screening.
ሰዓቴንም ማውለቅ ያስፈልገኛል? Do I need to take off my watch as well?
አዎ፣ እባክዎን የእጅ ሰዓትዎን ከኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎቹ ጋር ይጨምሩ። የተሳለጠ የደህንነት ፍተሻ እንዲናደርግ ይረዳናል።
Yes, please include your watch with the electronic devices. It helps us ensure a smoother security check.
ላፕቶፕዬን ከትንሹ ቦርሳዬ ውስጥ ማውጣት ይኖርብኛል?
Do I need to remove my laptop from my small suitcase?
አዎ፣ እባክዎን ላፕቶፕዎን ከሻንጣው ውስጥ አውጥተው ብቻውን ማስቀመጫ ውስጥ ያስቀምጡት። የበለጠ ግልጽ የሆነ የኤክስ-ሬይ ምስል እንዲኖር ያስችላል።
Yes, please remove your laptop from its bag and place it in a separate bin. It allows for a clearer X-ray image.
ገባኝ። እና ይህንን የውሃ ጠርሙስ ፣ ማሳለፍ እችላለሁ?
Got it. And this bottle of water, can i take it through?
አይ፣ ከማለፍዎ በፊት መጨረስ ወይም መጣል ይኖርብዎታል። ፈሳሽ አይፈቀድም። No, you’ll have to either finish it before going through or dispose of it. Liquids are not allowed.
እሺ፣ አሁን እጠጣዋለሁ። Okay, I’ll drink it now.
ትንሹ ሻንጣዬስ? What about my small suitcase?
ትንሹ ሻንጣ በኤክስ-ሬይ ማሽኑ ውስጥ ማለፍ አለበት። እባክዎን በማጓጓዣ ቀበቶው ላይ ያስቀምጡት።
The small suitcase needs to go through the X-ray machine. Please place it on the conveyor belt.
ገባኝ፣ ሌላ ማወቅ ያለብኝ ነገር አለ? Got it. Is there anything else I should aware of?
ዕቃዎችዎን ማሳለፍያው ማሽን ላይ እንዳደረጉ፣ የብረቱ መመርመሪያው በኩል ይለፉ። ድምጽ ከተሰማ፣ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ ያስፈልገን ይሆናል። Just walk through the metal detector once your items are on the belt. If it beeps, we may need to do an additional check.
ገብቶኛል፡፡ ለእርዳታዎ አመሰግናለሁ። Understood. Thank you for your help.
አሁን ከሁሉም ነገር ነጻ ነዎት፣ ወደ የመሳፈሪዎ በር መሄድ ይችላሉ። You’re all clear now, and you can proceed to your boarding gate.
ለእርዳታዎ እመሰግናለሁ። ወደ መሳፈሪያ በር እሄዳለሁ። Thank you for your help. I will make my way to the boarding gate now.
ወደ ኒውዮርክ የሚሄደው የበረራ ቁጥር ET152 አሁን በበር 23 ላይ እያሳፈረ ይገኛል። እባካችሁ ፓስፖርታችሁንና የመሳፈሪያ ካርዳችሁን አዘጋጁ። እናመሰግናለን።
Flight number ET152 to New York is now boarding at Gate 23. Please have your passport and boarding pass ready.
ክቡራን እና ክቡራት መንገደኞቻችን ከአዲስ አበባ ወደ ኒው ዮርክ ወደምናደርገው በረራ እንኳን ደኅና መጣችሁ።
Ladies and gentlemen, welcome abroad our flight from Addis Ababa to New York.
This is for today. If you enjoid this lesson, please share it with others who want to learn Amharic. Thanks a lot for your help.
You can share it by clicking on the share icon below. Also don’t forget to click on the “Complete Lesson” button.